EIN TECHNOLOGIES የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን #በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች የማዘመኑን ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል።
የህዝብ ግኑኝነት ክፍሎችን በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች የማዘመኑ ስራ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በዛሬው ዕለት #በአዲስ_አበባ ከተማ አስተዳደር የጉለሌ ክ/ከተማን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤትን #ዘመናዊና የተሳለጠ የህዝብ ግኑኝነት ሲስተም እንዲኖረው ለማድረግ የሚያስችል ሲስተምን ለመስራት ከክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ ተስፋዬ ኦሜጋ እና የክ/ከተማው የኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ከሆኑት ከአቶ ሽመልስ ጎዴቦ ጋር ባደረግነው ውይይት ከስምምነት ላይ ደርሰናል።
በዚሁ መሰረት የክ/ከተማውን የህዝብ ግኑኝነት #አሰራርን የሚያሳልጥ ዘመናዊ #ሲስተም የሚለማ ሲሆን ይህ ሲስተም የክ/ከተማውን ኮሙዩንኬሽን ጽ/ቤትን እና በስሩ የሚገኙትን #የአስሩንም ወረዳዎች አጠቃላይ ማህራዊ ሚዲያዎችንና ሌሎች መረጃዎችን በአንድ #ቋት አስተሳስሮ በመያዝ መረጃዎችን በቀላሉ ለህዝብ ተደራሽ የሚያደርግ ይሆናል።
ከሲስተም ማልማቱ ጎን ለጎን #ለክ/ከተማ አስተዳደሩ አመራሮች እና #ለብልፅግና ፓርቲ መሪዎች ስለ ሚዲያ አጠቃቀም እንዲሁም ፣ ለኮሙዩንኬሽን እና ለብልፅግና ፓርቲ ባለሙያዎች በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በማህበራዊ ሚዲያዎች አጠቃቀምና የደህንነት አጠባበቅ ፣ #በካሜራና#ኤዲቲንግ እና #በግራፊክስ መሰረታዊ የክህሎት ማስጨበጫ ስልጠና የሚሰጣቸው ሲሆን ስራው ሙሉ በሙሉ ተሰርቶ ሲጠናቀቅ የክ/ከተማውን የህዝብ ግኑኝነት ስራን የሚያዘምንና አንድ እርምጃ ወደ ፊት የሚያራምድ እንደሚሆን ይጠበቃል።
ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ የማድረግ ስራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል
EIN TECHNOLOGIES