#EIN_Technologies የደቡብ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የህዝብ ግኑኝነት ክፍልን ማዘመን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከዘርፉ አመራሮች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ
ሀዋሳ ፤ የካቲት 18/2014 ዓ.ም (EIN)
EIN Technologies የደቡብ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የህዝብ ግኑኝነት ክፍልን ማዘመን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከክልሉ ብ/ፓ/ጽ/ቤት የዘርፉ አመራሮች እና ከዞንና ልዩ ወረዳ ከመጡ የፓርቲው የሚዲያ ሀላፊዎች ጋር በሀዋሳ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
“የህዝባችንን የጉስቁልና ህይወት በአጭር ግዜ ቀይሮ ወደ ብልፅግና ማማ ለማድረስ የኮሙኒኬሽን አመራሩና ባለሙያው በቁጭት መነሳት አለበት” የሚል ዕሳቤን አንግቦ የተካሄደው ይህ መድረክ በዋናነት በዘርፉ የሚስተዋለውን ክፍተትና ውስንነትን መድፈን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን በዚህም መሠረት የነበሩት ጉድለቶች ተለይተውና በቀጣይ ተስተካክለው በተደራጀ አግባብ መረጃዎችን ወደ ህዝብ ተደራሽ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በቁጭት ለመስራት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
በዚሁ መሰረት #EIN_Technologies ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ጋር በመሆን የህዝብ ግኑኝነት ክፍሉን ለማዘመን የተለያዩ የቴክኖሎጂ ሲስተሞችን ለማልማት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ሲሆን ይህ ሲስተም ተገንብቶ ሲጠናቀቅ የፓርቲውን የህዝብ ግኑኝነት ክፍል አንድ ደረጃ ከፍ እንደሚያደርግ ይታመናል።