You are currently viewing EiN Technologies ለጋሞ ቴሌቪዥን የቴክኖሎጂ ክፍል ባለሙያዎች የግራፊክስና አኒሜሽን ስልጠና እየሰጠ ነው

EiN Technologies ለጋሞ ቴሌቪዥን የቴክኖሎጂ ክፍል ባለሙያዎች የግራፊክስና አኒሜሽን ስልጠና እየሰጠ ነው

የጋሞ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅ ዶ/ር አዲሱ አዳሙ ተቋሙ በተሻለ ጥራት ወደ ህዝብ ለመድረስ የተለያዩ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን አስታውሰው ስልጠናው ቴሌቪዥን ጣቢያውን ካለበት አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

በግራፊክስ እና አኒመሽን ዘርፍ ባለሙያ ማሟላት መቻሉን የጠቆሙት ዶ/ር አዲሱ አዳሙ፤ ዘርፉ ለሚዲያ ተቋም የጀርባ አጥንት በመሆኑ ባለሙያዎች ያላቸውን ክህሎት እንዲያጎለብቱ ይህ የተግባር ስልጠና ማስፈለጉን ተናግረዋል።

አክለውም ስልጠናው የባለሙያዎችን ክህሎት የሚያጎለብት ከመሆኑ ባሻገር ቴሌቪዥን ጣቢያው የያዘውን ጥራት ሳይለቅ እንዲቀጥል እንደሚረዳ በማስረዳት መሰል ስልጠናዎች ቀድመው እንደተሠጡና በቀጣይም እንደሚኖሩ አስገንዝበዋል።

#EiN_Technologies

Leave a Reply